Author name: siripn_admin

Partnership

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ”National Information Platform Nutrition (NIPN)” ፕሮጀክት ጋር በትብብር ለመስራት የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ፤

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፕሮጀክቱን ወደ ሲዳማ ክልል አውርዶ ለመስራት ግንቦት 22 /2016 ዓ.ም በሀዋሳ በተዘጋጀው ወርክሾፕ ላይ የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር መሳይ ኋይሉ በስምምነቱ ላይ እንደናገሩት ፕሮጀክቱ ከስርዓተ – ምግብ ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን ችግር በምርምር ለመፍታት የሚሰራ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ የተቀበለውን ሃላፊነት በተሻለ ደረጃ እየተወጣ እና ወደ ክልሎች ለማድረስ እየሰራ ነው ብለዋል። የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የስዳማ ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት ለማጠናከር እየሰራ ያለው ስራ ጥሩ መሆኑን ገልፀው ፕሮጀክቱ ክልሉ አብሮ እንዲሰራ እድሉ በመፈጠሩ ምስጋና አቅርበዋል። የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በክልሉ ከሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ የመስራት ፍላጎት እንዳለው ያስረዱት ዶ/ር ዳመነ የክልላችንን የስርዓተ – ምግብ ችግር ለመፍታት ልዩ ትኩረት ሰጥተን ተቋማትን አቀናጅተን በመስራት ውጤት እናመጣለን ብለዋል። በመድረኩ የፕሮጀክቱ አስተባባሪና መሪ ተመራማሪ ዶ/ር አረጋሽ ሳሙኤል በፕሮጀክቱ የሚከናወኑ ተግባራትን ያቀረቡ ሲሆን መረጃን መሰረት ያደረገ ውሳኔ እንዲሰጥ ተመራማሪዎችንና ውሳኔ ሰጪ አካላትን ማገናኘት የፕሮጀክቱ ዓላማ እንደሆነ አስረድተዋል። ዶ/ር አረጋሽ አክለውም ፕሮጀክቱን ወደ ሲዳማ ክልል በማውረድ ወደ ስራ ለማስገባት እንደሆነ ገልፀው ከዝህ በፊት ብዙ ውጤት እንደመጣ ገልፃ በሲዳማ ክልልም ጥሩ ውጤት እንድመጣ በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ተቋማት በቅንጅት በመስራት ሃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው። የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተቀበለውን ሃላፊነት መፈፀም እንደምችል እምነት እንዳላቸው የተናገሩት ዶ/ር መሳይ በጋራ በመስራት ለክልልም ሆነ ለአገር የሚጠቅም ስራ መስራት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል። በመጨረሻም በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር መሳይ ኃይሉ እና የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡ የስዳማ ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት 22/09/2016 ዓ.ም ሲዳማ/ሀዋሳ

Uncategorized

National Information platform Nutrition (NIPN) ፕሮጀክት ኃላፊዎች ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋራ ዉይይት አደረጉ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ ከዛምቢያ፤ ከኒጀር እና እና ከኢትዮጵያ የጀርመን ተራድኦ ድርጅት ማለትም የGIZ ፕሮጀክት የሆነውን “National Information platform Nutrition (NIPN) ፕሮጀክት ኃላፊዎችን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ከዚህ በፊት የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና ከ”National Information Platform Nutrition (NIPN)” ፕሮጀክት ጋር በትብብር ለመስራት የጋራ ስምምነት መፈራረማቸውና በክልል ደረጃ ይህ ፕሮግራም መጀመሩ ይታወሳል፡፡ ይህንን ለማጠናከርና የተለያየ ልምድ ልውውጥና ተሞክሮ ለመውሰድ ከዛምቢያ፤ ከኒጀር እና እና ከኢትዮጵያ የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች በሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመገኘት ሰፊ ውይይትና ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ በውይይቱ በሲዳማ ክልል ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት እና በሀዋሳ ዮኒቨርሲቲ በክልል ደረጃ እየተስራ ያሉ ሥራዎችና ጥናቶች ላይ ገለፃ ከተደረገ በኋላ በቀጣይ መስራት የሚገቡ ሥራዎች ላይ የበለጠ አብሮ ለመስራትና ፕሮግራሙን ለማጠናከር ከስምምነት ተደርሷል፡፡ የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥቅምት 21/2017ዓ.ም ሐዋሳ

fitness trainer 06
Uncategorized

Nutrition for Optimal Performance

Nutrition plays a pivotal role in athletic performance. What you eat before, during, and after you train can help improve your energy levels, increase your workout performance, and speed up recovery. Essential Nutrients for Athletes Hydration and Its Importance Hydration affects metabolic functions and energy levels. Water is essential for transporting nutrients, regulating body temperature, and digestion. Ensure you’re well-hydrated before, during, and after workouts to maintain performance and aid in recovery.

Scroll to Top