National Information platform Nutrition (NIPN) ፕሮጀክት ኃላፊዎች ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋራ ዉይይት አደረጉ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ ከዛምቢያ፤ ከኒጀር እና እና ከኢትዮጵያ የጀርመን ተራድኦ ድርጅት ማለትም የGIZ ፕሮጀክት የሆነውን “National Information platform Nutrition (NIPN) ፕሮጀክት ኃላፊዎችን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ከዚህ በፊት የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና ከ”National Information Platform Nutrition (NIPN)” ፕሮጀክት ጋር በትብብር ለመስራት የጋራ ስምምነት መፈራረማቸውና በክልል ደረጃ ይህ ፕሮግራም መጀመሩ ይታወሳል፡፡ ይህንን ለማጠናከርና የተለያየ ልምድ ልውውጥና ተሞክሮ ለመውሰድ ከዛምቢያ፤ ከኒጀር እና እና ከኢትዮጵያ የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች በሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመገኘት ሰፊ ውይይትና ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ በውይይቱ በሲዳማ ክልል ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት እና በሀዋሳ ዮኒቨርሲቲ በክልል ደረጃ እየተስራ ያሉ ሥራዎችና ጥናቶች ላይ ገለፃ ከተደረገ በኋላ በቀጣይ መስራት የሚገቡ ሥራዎች ላይ የበለጠ አብሮ ለመስራትና ፕሮግራሙን ለማጠናከር ከስምምነት ተደርሷል፡፡ የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥቅምት 21/2017ዓ.ም ሐዋሳ



